ለተስፋ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ:–
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣ 367(1) እና 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ (14) መሰረት የተስፋ ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 13ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ዋና ቢሮ ግቢ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል፤ ስለሆነም የተከበራችሁ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባኤው ላይ እንድትገኙልን የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ቀን፡ ህዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም
⏰ ሰዓት፡ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ
📍 ቦታ፡ በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤ/ን ዋና ጽ/ቤት ግቢ የመሰብሰቢያ አደራሽ
1. የማህበሩ ዋና ዋና መረጃዎች፡
1.1 የአክስዮን ማህብሩ ስም= የተስፋ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ
1.2 የአክስዮን ማህብሩ አይነት= በአነስተኛ የፋይናንስ ሰራ ላይ የተሰማራ
1.3 የማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ/ካፒታል/= 37,501,000.00 ብር
1.4 የማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ/ካፒታል/= 31,117,533.00 ብር
1.5 የማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት አድራሻ =አዲስ አበባ፤ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 547
1.6 የማህበሩ ንግድ ምዝገባ ቁጥር= KK/AA/3/0015717/2014
1.7 የማህበሩ ድህረ ገጽ፡ www.tesfamfisc.com
2. የ13ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፡
2.1 አጀንዎችን ማጽደቅ
2.2 አዳዲስ እና ነባር ባለአክስዮኖችን መቀበል እና ማጽደቅ (ከህዳር 16/03/2018 በፊት የተሸጡ)
2.3 እ.ኤ.አ 2025/26 ሂሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማፅደቅ
2.4 እ.ኤ.አ 2025/26 የውጭ ኦድተር አመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማፅደቅ
2.5 የውጭ ኦድተር መሰየም እና ክፍያውን መወሰን
2.6 እ.ኤ.አ የ2026/27 ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ወርሃዊ አበል እና አመታዊ የድካም ዋጋ መወሰን
2.7 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማካሄድ
2.8 እ.ኤ.አ 2025/2026 ሂሳብ ዓመት ትርፍና ኪሳራ አደላደል እና አከፋፈል ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ
2.9 የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ
3. ማሳሰቢያ
– ባለአክሲዮኖች ለስብሰባ በሚመጡበት ጊዜ ማንነትን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ የነዋሪነት መታወቂያ፣ የፋይዳ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይንም መንጃ ፍቃድ ዋናውን እና ቅጂውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፤
– በጉባኤ ላይ በአካል የማይገኙ ባለአክሲዮኖች በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሰረት በወኪሎቻቸው አማካይነት መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን፣ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ በመያዝ በተወካይ አማካይነት በጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ማንነትን የሚያሳይ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ የፋይዳ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ዋናውን እና ቅጂውን የወኪሉን የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ የፋይዳ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ቅጂ እንዲሁም፣ በጉባኤው ለመሳተፍ እና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ስልጣን ማስረጃ ዋናውን እና ቅጂውን ይዛችህ በመቅረብ በጉባኤው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡
ተስፋ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ
የዳይሬክተሮች ቦርድ
