የባለአክሲዮኖች የስብሰባ ጥሪ

ህዳር 19, 2019 ዓ/ም

የባለ አክሲዮኖች 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 5ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የጉባኤ ጥሪ

የተስፋ አነስተኛ የፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢ የገንዘብ ተቋም አ.ማ

የባለ አክሲዮኖች 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የጉባኤ ጥሪ

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)  367 (1) እና 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ መመሰረቻ ጽሁፍ 9(3) እና መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 12(2) መሰረት የተስፋ ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 13ኛ ዓመታዊ መደበኛ  ጠቅላላ ጉባኤ እና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ዋና ጽ/ቤት ግቢ በሚገኝ አዳራሽ ይካሄዳል ፡፡ ስለሆነም የተከበራችሁ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባኤዉ ላይ እንድትገኙ 

የዳሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋሉ፡፡

📅 ቀን: ህዳር 19 ቀን 2019 ዓ.ም
⏰ ሰዓት: ከ2:00 ሰዓት ጀምሮ
📍 ቦታ: በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ዋና ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አደራሽ

ለተጨማሪ መረጃ በ0970202070 ይደውሉ

ማሳሰቢያ

  1. በጉባኤው ላይ ለመገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሰረት ጉባኤዉ ከሚካሄድበት ቀን አስቀድሞ ባሉት ቀናት ውስጥ ማይክሮ ፋይናንሱ ዋና መስሪያ ቤት የአክሲዮን አስተዳደር ክፍል ወይም የተቋሙ ቅርንጫፎች በሉበት በመገኘት የውክልና ፎርም/ቅጽ በመሙላት ተወካይ በመወከል ወይም  በሰብሰባው ለመገኘትና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ማስረጃ ያለው ተወካይ ዋናውን እና አንድ  ፎቶ ኮፒ በጉባኤው እለት ይዞ እንዲቀርብ በማድረግ በወኪሎቻቸው አማካኝነት መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን ፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን መወከል የሚችለው አንድ ተወካይ ብቻ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  2. የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ በሚመጡበት ጊዜ የኢትዮጵያ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይንም ፋይዳ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውን ኮፒ መያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውን የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በአክብሮት እናሳውቃለን፡፤
  3. ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ ከሚደረግባቸው ጉዳዮችን ሌሎች የተቋሙ መረጃዎች ከተስፋ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ድረ-ገጽ ላይ በማውረድ መመልከት ወይንም አክሲዮን አስተዳደር ክፍል በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን አንገልጻለን ::

Scroll to Top